የአማራ ክልል ምክር ቤት 95 ነጥብ 31 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበውን የክልሉን መንግሥት የ2015 በጀት አጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 95 ነጥብ 31 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበውን የክልሉን መንግሥት የ2015 በጀት አጸደቀ፡፡
ምክር ቤቱ በጀቱን ያጸደቀው÷ በአንድ ድመፀ ተአቅቦ እና በአንድ ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ ነው፡፡
የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ጥላሁን መሐሪ የተያዘው በጀት የተለያዩ ጉዳዮችን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን በመጥቀስ፥ በህወሃት እና በኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም፣ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ለግብርና ኢንቨስትመንት፣ ለማዕድን ዘርፍ እና ለአካባቢ ጥበቃ ስራ ትኩረት መስጠቱን ጠቁመዋል።
በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን ችግር ምክንያት በማድረግ ለጋሽ ሃገራት ድጋፍ መቀነሱን ግምት ውስጥ ያስገባ ነው ብለዋል።
በጀቱ ከባለፈው ዓመት በጀት ጋር ሲታይ 19 በመቶ ብልጫ አለው።
በአሁኑ ሰዓት ከምክር ቤቱ የተለያዩ ሃሳቦች እየቀረበበት ነው።
በምንይችል አዘዘው