የመጀመሪያው የፌዴራል ጠበቆች ማኅበር አስተዳደር ቦርድ ተመሠረተ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነው የፌደራል የጠበቆች ማህበር አስተዳደር ቦርድ ዛሬ ተመስርቷል፡፡
በሕግ እና በሕግ ብቻ የሚመራ የጠበቆች ቦርድ ማቋቋምአስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነው የፌደራል የጠበቆች ማህበር አስተዳደር ቦርድ ሊመሰረት እንደቻለ ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ የፍትሕና የጥብቅና ስርዓትን ያዘምናል ተብሎ የታመነበት ቦርዱ ተጠሪነቱ ለፍትህ ሚኒስቴር እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡
የቦርዱ ስራ አስፈፃሚ አባላት ዛሬ የመጀመሪያውን ውይይት ከሚኒስቴሩ አመራሮች ጋር ያካሄዱ ሲሆን ÷ከነገ ጀምሮ ቦርዱ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንደሚገባ ታውቋል፡፡ ፡፡
በኢትዮጵያ ሁለት የጠበቆች የሙያ ማህበራት ቢኖሩም በቦርድ ደረጃ ሲቋቋም ይህ የመጀመሪያ ነው ።
ማህበሩ በፌደራል ደረጃ በጥብቅና ሙያ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች አባል የሚሆኑበት እንደሆነ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።