Fana: At a Speed of Life!

ዩኒቨርሲቲዎች የንድፈሃሳብ ልህቀት ብቻ ሳይሆን የተግባር ልህቀትም ማምጣት ይጠበቅባቸዋል-አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩኒቨርሲቲዎች የንድፈሃሳብ ልህቀት ብቻ ሳይሆን የተግባር ልህቀትንም ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም አደም ፋራህ ገለጹ፡፡
 
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሶስተኛውን የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።
 
በመድረኩ የዕለቱ የክብር እንግዳ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳቢና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉን አቀፍ ልህቀት ማምጣት አለባቸው ብለዋል።
 
ዩኒቨርሲቲዎች ለለውጥና ለሀገር ሁለንታዊ ብልጽግና ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ ነው ያሉት አቶ አደም መንግሥትም ለዩኒቨርሲቲዎች ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው ብለዋል።
 
ዩኒቨርሲቲዎች ለማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንባታ ትኩረት ሰጥተው መሥራት ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉትአቶ አደም÷ ዩኒቨርስቲዎች የንድፈሃሳብ ልህቀት ብቻ ሳይሆን የተግባር ልህቀትም ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
 
በመማር ማስተማር ፣በምርምርና በማኅበረሰብ አገልግሎት ብቻም ሳይሆን በተቋም አመራር ፣በፋይናንስ አስተዳደር ላይም ልህቀት ያስፈልጋል ሚናችሁም ከፍተኛ መኾን አለበት ሲሉም አሳስበዋል።
 
በተለይም በግዥና ፋይናንስ፣ በንብረት አስተዳደር ላይ ወሳኝ ሚና መጫውት እንዳለባቸው ነው የተናገሩት።
 
የሀገሪቱ ትላልቅ ፕሮጀክቶች የሚስተዋልባቸውን ሁሉን አቀፍ ተግዳሮት የሚፈታ ሚና መጫወትም አለባቸው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
 
‟መንግሥት ከሚደጉማችሁ በተጨማሪ ሃብት በመፍጠርና ሃብትን በአግባቡ ማስተዳደር ላይ ልህቀት እንድታመጡ መሥራት ይጠበቅባችኋል” ብለዋል።
 
ዩኒቨርሲቲዎች ሀገር የሚገነቡ ሃሳቦች የሚፈልቁባቸው እንጂ ሀገር የሚያፈርሱ ሃሳቦች የሚመንጭበት እንዳይሆን መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል።
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.