Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ ከ888 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባቸውን መጸዳጃ ቤቶች አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከ 888 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባቸውን 62 መጸዳጃ ቤቶች ዛሬ ለጤና ቢሮ፣ ለትምህርት ቢሮ እና ለወረዳዎች አስረክቧል፡፡
ባለስልጣኑ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ያስገነባቸው መጸዳጃ ቤቶች በትምህርት ቤት፣ በጤና ጣቢያዎች እና ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ከሆኑት መካከል 24ቱ በትምህርት ቤቶች እንዲሁም 21ዱ በጤና ጣቢያዎች የተገነቡ ሲሆን÷ የተቀሩት 17ቱ ደግሞ የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡
መጸዳጃ ቤቶቹ የማህበረሰቡን የንፅህና አጠባበቅ ባህል በማሻሻልና የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓቱን በማሰተካከል ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር በጎ አስተዋፅኦ እንደሚኖራቸውም ተገልጿል፡፡
መጸዳጃቤቶቹ የአካል ጉዳተኞችን ታሳቢ አድርገው የተገነቡ ሲሆን÷ ከዚህ በተጨማሪ የሻወር፣ የፅዳት ሠራተኞች ክፍል፣ የእጅ መታጠቢያ እንዲሁም በጤና ጣቢያ የተገነቡት የቆሻሻ ማቃጠያ እና ማስወግጃን ያካተቱ ናቸው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.