Fana: At a Speed of Life!

በህገ ወጥ መንገድ ወደ ትግራይ ክልል ሊገባ የነበረ ከ8 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ብር ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰብዓዊ እርዳታ በጫነ ተሽከርካሪ ውስጥ ተደብቆ ወደ ትግራይ ክልል ሊገባ የነበረ ከ 8 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ብር ተያዘ፡፡

ህገ ወጥ ገንዘቡ በአፋር ክልል በኩል ወደ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ይዞ በመጓዝ ላይ ከነበረ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪ መኪና ውስጥ ነው የተያዘው፡፡

የከባድ ጭነት ተሽከርካሪ መኪናው መነሻውን ከአዲስ አበባ አድርጎ የሰብዓዊ የምግብ ድጋፍ በመያዝ እና በውስጡም የተጠቀሰውን ጥሬ ገንዘብ እና ሌሎች ያልተፈቀዱ ዕቃዎች በህገወጥ መንገድ ወደ ትግራይ ክልል ለማሳለፍ ሲሞክር በሰርዶ የፍተሻ የጣቢያ መያዙ ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም በተደረገው ፍተሻ የብር የአንገት ሃብሎች እና ሌሎች ህገወጥ እቃዎች መያዛቸውን በሰርዶ የፍተሻ ጣቢያ የፌዴራል ፖሊስ አባል የሆኑት ኢንስፐክተር አብዱሮህማን ሀሰን መናገራቸውን ከአፋር መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.