ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ለቻይና የመከላከያ ሠራዊት የምስረታ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የቻይና የመከላከያ ሰራዊት የተመሰረተበትን 95ኛ ዓመት ክብረ በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ በመልዕክታቸው÷ የቻይና የመከላከያ ሰራዊት የሀገሩን ሉዓላዊነት፣ ጸጥታና ጥቅም ከማስከበር አልፎ ለዓለማችን ሰላምና መረጋጋት እያደረገ ላለው በጎ ሚና ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ÷ቻይና እና ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት የዘለቀ ታሪካዊ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አውስተዋል፡፡
በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በመመስረት በሀገራቱ መካከል ያለው ግንኙነት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በባህል፣ በትምህርት እና በጤና መስኮች ከፍተኛ ዕድገት እያሳየ እንደመጣ መግለጻቸውንም ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ሁለቱ ወዳጅ ሀገራት በወታደራዊ ዲፕሎማሲና ትብብር ላይ ከፍተኛ ዕድገት ላይ እንደደረሱ ጠቁመው ÷ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!