Fana: At a Speed of Life!

ተቋማቱ በምርምርና በሰው ኃይል ልማት በትብብር ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በምርምርና በሰው ኃይል ልማት በትብብር ለመሥራት የሚያስችል የጋራ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

በተጨማሪም የትብብር ስምምነቱ÷ በቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ማልማት፣ በምርምር እና ልማት፣ በሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ የሰው ኃይል ልማት እንዲሁም ፕሮጀክቶችን በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና ገልጸዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ኮማንዳንት ሜ/ጀኔራል ሃብታሙ ጥላሁን እንደገለጹት÷ ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት ያላቸውን የሰው ኃይል እና ሃብት በቅንጅት በመጠቀም ለሀገራዊ ስኬት በጋራ ለመሥራት ያስችላቸዋል፡፡

ስምምነቱን ተፈፃሚ ለማድረግ ከሁለቱ ተቋማት የቴክኒክ ኮሚቴ ተደራጅቶ ወደ ሥራ መግባቱን የመከላከያ ሠራዊት  መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.