Fana: At a Speed of Life!

የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እስከ ነሐሴ 13 እንዲመዘገቡ ባለሥልጣኑ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢሰ ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች እስከ ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ አመልክተው ፈቃድ እንዲወስዱ ጥሪ አቀረበ።

የመገናኛ ብዙኃን አዋጁ ህብረተሰቡ የሃይማኖት ፕሮግራሞችን ለመከታተል ያለውን ፍላጎት በመገንዘብ የሃይማኖት ድርጅቶች አስተምህሮታቸውን በመገናኛ ብዙኃን እንዲያደርሱ የብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡

ስለሆነም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁ.1238/2013 አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 3/ለ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ከሰኔ 27/2014 ዓ.ም ጀምሮ የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን እየመዘገበ እንደሆነ ጠቅሷል፡፡

በዚህም መሰረት ማንኛውም የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያ እስከ ነሐሴ 13/2014 ዓ.ም ድረስ https://www.eservices.gov.et/ በሚለው ፖርታል ውስጥ በመግባት ወይም በአካል በመቅረብ ማመልከትና ፈቃድ መውስድ እንዳለበት ከባለሥልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.