ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ የራሱንና የቤተሰቡን ጤና እንዲጠብቅ አሳሰቡ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ የራሱን እና የቤተሰቡን ጤና እንዲጠብቅ አሳሰቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መገኘቱን በማስመልከት ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ ራሱን እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው እጅን በውሃ እና በሳሙና አዘውትሮ መታጠብ፣ የጉንፋን ምልክት ከታየ ከቤት አለመውጣት፣ ሰው የሚበዛብት ቦታ አለመሄድ፣ ንክኪ የሚያስፈልጋቸው የሰላምታ መንግዶችን መተው፣ ሰው በብዛት የሚሰበስባቸው ቦታዎች ላይ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እና ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ በንቃት የራሱን እና የቤተሰቡን ጤና መጠበቅ እንዳለበት መልዕክታቸውን በፌስ ቡክ ገፃቸው አስተላልፈዋል፡፡