Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለዩክሬን የ3 ቢሊየን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ ልታደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለዩክሬን ተጨማሪ 3 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ወታደራዊ ድጋፍ ይፋ ልታደርግ መሆኑን አስታውቃለች፡፡

ድጋፉ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ ከገባችበት ጊዜ ወዲህ ዋሺንግተን ለኪዬቭ ካደረገቻቸው ወታደራዊ ድጋፎች ከፍተኛ መጠን ያለው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ወታደራዊ ድጋፉ ከዩክሬንን የነጻነት ቀን ጋር እንዲገጣጠም ለማድርገ መታቀዱንም ሬውተርስ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

የእርዳታ ማዕቀፉ አሜሪካ ለዩክሬን ከመደበችው የዩክሬን ደህንነት እርዳታ ኢኒሼቲቭ በጀት ወጪ የሚደረግ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

አሜሪካ ከዚህ በፊት ለዩክሬን የተለያየ መጠን ያለው የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማድረጓ የሚታወስ ነው፡፡

የአሁኑ ድጋፍ ከጦር መሳሪያ ባለፈ ዩክሬንን የመከላከያ አቅም መገንባት የሚያስችል የመካከለኛ ጊዜ እቅድን ያካተተ መሆኑም ነው የተገለጸው።

የጦር መሳሪያ ድጋፉም አሜሪካ ከዚህ ቀደም ካደረገችው የተለየ እንደሆነም ነው ስማቸው ያልተጠቀሰው ባለስልጣን የገለጹት።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.