የኢትዮጵያና ካሜሮን አምራቾች ትሥሥር የሚፈጥሩበት መድረክ መመቻቸቱ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያና ካሜሩን አምራቾች ልምድ የሚለዋወጡበት እና የዕውቀት ሽግግር የሚያደርጉበት ትሥሥር ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የካሜሮን-ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ቻምበር ፕሬዚዳንትና ልዑካን ቡድናቸው የቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝተዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑን የመሩት የካሜሩን ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቻምበር ፕሬዚዳንት አቦሶሎ ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነዋል፡፡
የሀገራቱ እንዲሁም ሌሎች አምራቾች በዘርፉ ትሥሥር እንዲፈጥሩም የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ነው ያረጋገጡት፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ኩባንያዎች በፈረንጆቹ ታኅሣሥ ወር በካሜሩን በሚካሄደው የኢኮኖሚ ቻምበር እንዲሳተፉ ፕሬዚዳንቱ ጥሪ ማቅረባቸውን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።