ትዴፓ አሸባሪው ህወሓት በህዝብና ሀገር ላይ የጀመረውን ጦርነት አወገዘ
አበባ ፣ ነሐሴ 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) አሸባሪው ህወሓት በህዝብና አገር ላይ የጀመረውን የሶስተኛ ጊዜ ጦርነት በጽኑ አውግዟል።
ትዴፓ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባወጣው መግለጫ÷አሸባሪው ህወሓት ተቀባይነት የማይኖራቸው ቅድመ ሁኔታዎችን በመደርደር የሰላም አማራጭ እንዳይሳካ ማድረጉን አንስቷል፡፡
አሸባሪው ህወሓት ጸረ ሰላም መሆኑንና ለህዝብም ደንታ እንደሌለው፣ ዘራፊና አሸባሪ ስለመሆኑ መላው ዓለም መገንዘቡን ፓርቲው በመግለጫው አመላክቷል።
ጦርነቱን እንደጀመረ የፈጸመው የ570 ሺህ ሊትር በላይ የነዳጅ ዝርፊያ ጸረ ህዝብ መሆኑን ያሳየበት ተግባር መሆኑንም ጠቅሷል።
አሸባሪው ህወሓት በህዝብና ሀገር ላይ የጀመረውን ጦርነት ያወገዘው ትዴፓ÷ በጦርነቱ ለሚደርሰው ጥፋት ሁሉ ተጠያቂው ህወሓት እንደሆነ ገልጿል።
ፓርቲው መንግስት የሀገርንና የህዝብን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚወስደውን እርምጃ እንደሚደግፍ ገልጾ÷ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚጠበቅበትን እንደሚወጣም አረጋግጧል።
መላው ኢትዮጵያዊ በዚህ አገርን የማስከበርና የህዝብን ደህንነት የማረጋገጥ እርምጃ ከመንግስት ጎን እንዲሰለፍ ጥሪ ማቅረቡን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
እንዲታጠቅ የተገደደውና ለግለሰቦች የስልጣንና የጥቅም ፍላጎት በማለቅ ላይ ያለው ወጣትም በተመቸው መንገድ አፈሙዙን ወደ ጨቋኞቹ የህወሓት አመራሮች እንዲያዞር ወይም በሰላም እጁን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል እንዲሰጥ ትዴፓ መልዕክቱን አስተላልፏል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!