የፖለቲካ ፓርቲዎች በአከባቢ ምርጫ ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ምርጫ ቦርድ ጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ፣ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፖለቲካ ፓርቲዎች በአከባቢ ምርጫ ላይ በንቃት እንዲሳተፉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጠይቋል።
ምርጫ ቦርድ ለ5ኛ ጊዜ በሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ የሕግ ማዕቀፍ እና አፈጻጸም ላይ ያስደረገውን ጥናት አስመልክቶ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምክክር አካሂዷል።
በኢትዮጵያ የአካባቢ ምርጫን ለማካሄድ ያለው የሕግ ማዕቀፍ በጥናቱ የተመላከተ ሲሆን÷ ክልሎች ሕገ-መንግሥቱን መሠረት በማድረግ በተለያዩ ጊዜ ምርጫ ማካሄዳቸው በጥናቱ ተነሥቷል።
5ኛውን የአከባቢ ምርጫ ከክልሎች ጋር በመነጋገር በ2015 ዓ.ም እንደሚደረግም የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ ተናግረዋል።
የአካባቢ ምርጫ የብሔረሰብ፣ የዞን፣ የወረዳ እና የቀበሌ ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ የሚካሄድበት እንደሆነ በምርጫ ህጉ ተቀምጧል፡፡
በኢትዮጵያ ቀደም ሲል 4 የአከባቢ ምርጫዎች የተካሄዱ ሲሆን÷ የመጨረሻው ከተካሄደ ከ9 ዓመት በላይ እንዳስቆጠረ መገለጹን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!