77ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ በኒው ዮርክ መካሄድ ጀመረ።
ጉባዔው “ወሳኝ ወቅት ለተሳሰሩ ችግሮች ለውጥ አምጪ መፍትሔዎች” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ ያለው፡፡
በጉባኤው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፥ አባል ሀገራት የጋራ ፈተናዎችን ለመፍታት እንዲተባበሩ ጠይቀዋል።
ከጉባኤው ጎን ለጎን ትምህርት፣ የዘላቂ ልማት ግቦች፣ ሰብአዊ መብት፣ የኒውክሌር መሳሪያ አጠቃቀምን ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የሚመክር መድረክ እንደሚኖር ሺንዋ ዘግቧል።
ጠቅላላ ጉባዔ በአካልና በበይነ መረብ የሚካሄድ ሲሆን እስከ መስከረም 17 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚቆይ ተመላክቷል፡፡