ኤጀንሲው የመዲናዋን የትራፊክ ፍሰት የሚያሻሽሉ ስራዎችን እየሰራሁ ነው አለ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የትራፊክ ፍሰት የሚያሻሽሉ ስራዎችን እየሰራሁ ነው ሲል አስታወቀ፡፡
ወቅቱ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ተቀብለው የሚያስተምሩበት ወቅት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ኤጀንሲው ተለዋዋጭ የትራፊክ ፍሰት ሁኔታን ባገናዘበ መልኩ የትራፊክ መጨናነቅን በተለየ ሁኔታ ፍሰቱን ለማሻሻል እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡
በኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ኤልያስ ዘርጋ ፥ በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚፈጠሩ የፍሰት መጨናነቅ ችግሮች እንዲፈቱ ከትምህርት ቤቶች ማህበረሰብ ጋር ተወያይቶ መግባባት ላይ ደርሷል ነው ያሉት፡፡
በተጨማሪም የትምህርት ቤቶች መግቢያና መውጫ በሮች የአካባቢውን የትራፊክ ፍሰት በማያውክ መልኩ እንዲስተካከሉ እየተደረገ መሆኑን መግለጻቸውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በትምህርት ቤቶች አካባቢ ኤጀንሲው እያደረጋቸው ከሚገኙ የማሻሻያ ስራዎች ምልክትና ማመላከቻዎች መትከል፣ አሽከርካሪዎች አካባቢው ላይ ባሉ አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀሙ በማድረግ ከዋናው መንገድ ገባ ባሉ ስፍራዎች ተሳፋሪዎቻቸውን እንዲጭኑና እንዲያወርዱ የታክሲ መጫኛና ማውረጃ ቦታዎችን የማሸጋሸግና ሌሎች ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙም ነው የተናገሩት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!