Fana: At a Speed of Life!

12ኛው የጣና ፎረም ጉባዔ በጥቅምት ወር ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጣና ፎረም በመጪው ጥቅምት ወር አጋማሽ በባሕርዳር ከተማ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

የ2015 ዓ.ም ጣና ፎረም ጉባዔ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አስመልክቶ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ከጣና ፎረም አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር ተወያይተዋል።

ጣና ፎረም ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ በአፍሪካ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መፍትሔ ለማፈላለግ የተቋቋመ እና በአፍሪካ ኢኮኖሚ፣ ሰላም፣ ንግድ ትስስር እና የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም ዙሪያ የሚመክር አፍሪካዊ ነጻ ተቋም ነው፡፡

የአፍሪካ መሪዎች በአፍሪካ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረው አቅጣጫ የሚያስቀምጡበት ጣና ፎረም በየዓመቱ በባሕርዳር ከተማ እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡

ከ250 በላይ የሚሆኑ አፍሪካውያን የፎረሙ ተሳታፊዎች ስለ አህጉራዊ ጉዳዮቻቸው ተገናኝተው ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.