በመዲናዋ አማኑኤል አካባቢው በጎርፍ አደጋ የወደሙ ቤቶች ግንባታ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አማኑኤል አካባቢ በተፈጥሮ አደጋ የመኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች ዛሬ የመልሦ ግንባታ ሥራ ተጀምሯል፡፡
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ በመልሦ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት÷ ከተማ አስተዳደሩ ሰው ተኮር ሥራዎችን እየሠራ ነው፡፡
ጉዳት ከመድረሱ በፊት ቅድመ መከላከል ላይ ያተኮረ ሥራ እንደሚሠራም አስታውቀዋል።
የኢንዱስትሪ ሚንስትር መላኩ አለበል በበኩላቸው÷ ሚንስቴሩ በተፈጥሮ አደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች የ100 ሺህ ብር ስጦታ አበርክቷ ማለታቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
በአደጋው የወደሙትን 10 ቤቶችም ሙሉ በሙሉ ገንብተው እንደሚያስረክቡ አረጋግጠዋል፡፡
አማኑኤል አካባቢ ሐምሌ 24 ቀን 2014 ዓ.ም በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሁለት ሰው ሕይወት ማለፉ እና 10 ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ይታወሳል፡፡