Fana: At a Speed of Life!

አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ከአሜሪካ ሴናተሮች ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቶ ታገሠ ጫፎ የአሜሪካ ሴናተሮችን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

አቶ ታገሠ ጫፎ በአሜሪካ ሴናተር የወታደራዊ አገልግሎት ኮሜቴ ሊቀመንበር ሚስተር ጀምስ ኢንሆፍ ከተመራው ጆን ሞዝማን እና ማስተር ማሪዮን ማይክ የተካተቱበት የልዑካን ቡድን ጋር ነው የተወያዩት፡፡

በዚሁ ወቅት አፈ-ጉባዔው በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች እና በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙት ዙሪያ ለልዑካን ቡድኑ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያን እና የአሜሪካን የሁለትዮሽ የወዳጅነት ግንኙነት ለማጠናከር እንዲሁም ፓርላሜንታዊ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጎልበት በትብብር የሚሰራ መሆኑንም ነው ያስረዱት፡፡

ሚስተር ጀምስ በበኩላቸው ፥ አፈ-ጉባዔው በሰጡት ማብራሪያ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ የሁለቱ ሀገራት የፓርላሜንታዊ ግንኙነት ላይ በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ማረጋገጣቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.