“የምትፈተኑት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለኢትዮጵያ እውነተኛ ተስፋዎች መሆናችሁን የምታረጋግጡበት እንደሚሆን አምናለሁ” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “የምትፈተኑት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለኢትዮጵያ እውነተኛ ተስፋዎች መሆናችሁን የምታረጋግጡበት እንደሚሆን አምናለሁ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለዘንድሮ ተፈታኞቾ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የሀገራችን የነገ ተስፋዎች ያሏቸው ተፈታኞቹን፥ “ኢትዮጵያ እናንተን ስታይ ተስፋ ነው የሚታያት” ብለዋል።
“እናንተን እዚህ ለማድረስ ወላጆች፣ መምህራን እና መላው ማኅበረሰብ ለዓመታት ለፍቷል” ነው ያሉት።
“ውጤቱን የምታሳዩት ከኩረጃና ከስርቆት ነጻ ሆናችሁ፣ በራሳችሁ ተማምናችሁ፣ ፈተናውን ስትፈተኑ ነውም” ብለዋል።
“የተሰጣችሁን መመሪያ አክብሩ፤ ተረጋግታችሁ ፈተናችሁን ሥሩ፤ በምንም አትሸበሩ፤ የኢትዮጵያ አምላክ ዕውቀቱን ይግለጥላችሁ” ሲሉም አሳስበዋል።