በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ዋሺንግተን ዲሲ ገባ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዋሺንግተን ዲሲ ገብቷል።
ልዑኩ በቆይታው በዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ዓመታዊ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገኖች ውይይት ላይ ይሳተፋል ተብሏል።
ቡድኑ በዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የመጀመሪያው ውይይት ማድረጉን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሲለሺ በቀለ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!