ኢትዮጵያ ባለ ልዩ ጣዕም ቡናን በዓለም አቀፍ የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ኤግዚቢሺን ላይ አስተዋወቀች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ባለ ልዩ ጣዕም ቡናን ጃፓን በተካሄደው ዓለም አቀፍ የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ኤግዚቢሺን ላይ አስተዋውቃለች፡፡
ከጥቅምት 11 እስከ 14 ቀን በቶኪዮ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ኤግዚቢሺን እና ጉባኤ ላይ በርካታ ቡና አምራቾች፣ ላኪዎች አና አስመጪዎች ምርቶቻቸውን ለዕይታ አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ ከ40 በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች፣ የኢትዮጵያ ቡና ማህበር እና የኢትዮጵያ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራትም ነው የተሳተፉት፡፡
በኤግዚቢሽኑም የኢትዮጵያን ባለ ልዩ ጣዕም ቡና በተለያዩ መንገዶች በተሳካ ሁኔታ ማስተዋወቅ መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡
በመድረኩ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎችም ከጃፓን ቡና ላኪዎች እና ከሌሎች ሀገራት ላኪዎች ጋር በዘርፉ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳች ላይ መምከራቸው ተጠቁሟል፡፡
በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው÷ ቀዳሚ የቡና ላኪ ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ ከዘርፉ የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ ምርቱን የማስተወቅ ስራ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ማንሳታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!