Fana: At a Speed of Life!

በሱዳን በተፈጠረ የጎሳ ግጭት 150 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምስራቅ ሱዳን በተፈጠረ የጎሳ ግጭት በሁለት ቀናት ውስጥ በትንሹ 150 ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት ውስጥ በተፈጠረው የጎሳ ግጭት ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ በርካታ ቁጥር ያላቸው ደግሞ መቁሰላቸውን የሀገሪቱን ሚዲያዎች ዋቢ አድርጎ አናዶሉ ዘግቧል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በለጋዋ የተከሰተው አመፅ መባባስ እና በብሉ ናይል ክልል እንደ አዲስ የተከሰተው የግጭት እንዳሳሰበው ገልጿል።

የሀገሪቱን ህዝብ ፍላጎት ቅድሚያ የሚሰጥ እና ደህንነቱን የሚጠብቅ፣ ለግጭት መንስኤዎች መፍትሔ የሚያመጣ አስተማማኝ መንግሥት ከሌለ ዘላቂ ሰላም ማግኘት ከባድ መሆኑንም ነው የገለጸው።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.