ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳና ቦራ ወረዳ በኩታ ገጠም የለማን የስንዴ ማሳ ጎበኙ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳና ቦራ ወረዳ በኩታ ገጠም ለምቶ እየተሰበሰበ ያለን የስንዴ ማሳ ጎብኝተዋል።
በወረዳው ስምንት ሺህ አርሶ አደሮች በኩታ ገጠም ግብርና 31 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ በስኬታማነት ስንዴን ማምረታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
“በህብረት ስንሠራ የምግብ ዋስትና ግባችን ይሳካል፣ ፈተናዎቻችንን ድል እንነሳለን፣ ሀገራችንም ትለማለች” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።