Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ጸንታ የቆመችው ሕይወታቸውን ሳይሰስቱ የሚሰጡ ጀግኖች ስላሏት ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ጸንታ የቆመችው ሕይወታቸውን ሳይሰስቱ የሚሰጡ ጀግኖች ልጆች ስላሏት ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን በፖሊሳዊ አገልግሎት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሰራዊቱ አመራሮችና አባላት የዕውቅናና ማበረታቻ ሥነ ስርዓት አካሂዷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ ጸንታ የቆመችው ሕይወታቸውን ሳይሰስቱ የሚሰጡ ጀግኖች ልጆች ስላሏት ነው ብለዋል፡፡

አክለውም የኢትዮጵያን ቀጣይነት ሁሌም በጀግኖች ልጆቿ ውስጥ እንመለከታለን ነው ያሉት፡፡

ፖሊስ በቴክኖሎጂ፣ በአደረጃጀት እና ተደራሽነቱን በሚፈለገው አግባብ እያሰፋ እንዲሄድ ዘርፈ ብዙ ጥረት እያደረግን እንገኛለን ብለዋል፡፡

ይህም በሁሉም ረገድ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ጠላቶቻችን በጦር ግንባር ያጋጠማቸውን ኪሳራ አዲስ አበባ ላይ ለማካካስ ያደረጉትን ጥረት በማክሸፋችሁ የአዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮችና አባላት ለከፈላችሁት ዋጋ ሁሉ ዕውቅናና ምስጋና ይገባችኋል ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እንደገለጹት÷ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከጸጥታ ተቋማት እና ህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት የመዲናዋን ሰላም አስጠብቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.