Fana: At a Speed of Life!

በመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት መታሰቢያ የፊታችን ሐሙስ በአፋር ክልል ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት መታሰቢያ “መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ሐሳብ በአፋር ክልል ደረጃ ሐሙስ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ታስቦ ይውላል፡፡

መታሰቢያው የሚካሄደው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የጀግንነትና የመስዋዕትነት ምልክት ተደርጎ መወሰድ ስላለበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ በአሸባሪው ህወሓት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም መወጋቱ ይታወሳል፡፡

በክልል ደረጃ መታሰቢያው ሲካሄድ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ለሀገራቸው የከፈሉትን መስዋዕትነት በማሰብ ነው መባሉን የአፋ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

የአፋር ሕዝብ ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመሆን መስዋዕትነት መክፈሉም ነው የተገለጸው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.