Fana: At a Speed of Life!

የደንበኞችን የእርካታ ደረጃ በሚያሳድጉ ስትራቴጂክ ሥራዎች ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደንበኞችን የዕርካታ ደረጃ ሊያሳድጉ በሚችሉ ስትራቴጂክ ሥራዎች ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአገልግሎቱ የመስክ ምልከታ አድርገዋል፡፡

የሥራ ሃላፊዎቹ የመስክ ምልከታውን ያደረጉት በአገልግሎቱ ማዕከላዊ ዕቃ ግምጃ ቤት፣ የመረጃ ማዕከል፣ የአቃቂ ቃሊቲ ቁጥር 1 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያና በምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 6 የአገልግሎት መስጫ ማዕከል ነው፡፡

በመስክ ምልከታው የተሳተፉ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የሥራ ሃላፊዎች ፥ ተቋሙ እያከናወናቸው የሚገኙ መልካም ስራዎችን አድንቀው ፤ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ማሞ ምኅረቱ ተቋሙ የደንበኞችን የእርካታ ደረጃ ሊያሳድጉ በሚችሉ ስትራቴጅክ ስራዎች ላይ ትኩረት ሊያደርግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ እንዳሉትም ፥ ተቋሙ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመለየት የደንበኞችን የእርካታ ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

በቀጣይም ተቋሙ የተጣለበትን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣትና ለደንበኞች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ከተቋሙና ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ መግለጻቸውን ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.