በተሰጣቸው የንግድ ፍቃድ መሠረት ባልሰሩ 19 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በተሰጣቸው የንግድ ፍቃድ መሠረት ባልሰሩ 19 ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በ206 ድርጅቶች ላይ ባደረገው የድህረ ፈቃድ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ተግባር 19 የሚሆኑት ድርጅቶች በተሰጣቸው የንግድ ፍቃድ መሠረት እየሰሩ አለመሆኑ ተመላክቷል፡፡
በዚህም በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ በተደረገው ማጣራት በ11 ድርጅቶች ላይ የንግድ ስራ ፍቃድ እግዳ በስምንቱ ላይ የጽሁፍ ማስጠንቀቅያ እርምጃዎች ተወስዶባቸዋል፡፡
በአንጻሩ 187 ድርጅቶች በህግ አግባብ መሠረት እየሰሩ መሆኑ መረጋገጡን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡