Fana: At a Speed of Life!

የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚያደርግ የሶማሌ ክልል ገለጸ

አዲ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በነበረው ችግር የተጎዱ ወገኖችና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የሶማሌ ክልል አስታወቀ።

የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ በሺር ሼኽ ሰዒድ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ በመንግስትና በህወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ በቅርቡ ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት ክልሉ የድርሻውን እንደሚወጣ ገልጸዋል።

የተደረሰው የሰላም ስምምነት አፍሪካውያን ችግሮችን በራሳቸው መፍትሄ መስጠት እንደሚችሉ ማሳያ መሆኑን አመላክተዋል።

የሰላም ስምምነቱ ፋይዳና አስፈላጊነት የክልሉ ነዋሪዎች በቂ ግንዛቤ ይዘው ለተግባራዊነቱ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ የሚረዳ መድረክ ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በመድረኩ የመንግስት ሰራተኞች፣ የባህላዊ መሪዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ሴቶችና ወጣቶችን ጨምሮ ሌሎችም ነዋሪዎች እንደሚሳተፉ ጠቁመዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.