Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር ኤርጎጌ በተመድ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና የሴቶች ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና የሴቶች ዳይሬክተር ማክሲም ሁዋኔቶ ጋር ተወያዩ፡፡

ዶክተር ኤርጎጌ÷ የሴቶችን መብት ለማስከበር፣ የስርዓተ ፃታ እኩልነትን ለማስፈን፣ ብቃትና ተጠቃሚነትታቸውን ለማረጋጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር እያከናወኗቸው ያሉ ተግባራትን አብራርተዋል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች ተፈናቅለው በመጠለያ ለሚገኙ ሴቶች ሰብዓዊ ድጋፎችን ተደራሽ ከማድረግ ጎን ለጎን÷ ጥቃት የደረሰባቸው ወገኖች የአንድ ማዕከል፣ የማረፊያና ማገገሚያ በማቋቋም ሁለገብ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉንም አስረድተዋል፡፡

በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ለማስቻል ያለመ ፕሮጀክት ተነድፎ ወደስራ ተገብቷል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የተጀመሩ ተግባራት ስኬታማ እንዲሆኑ የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡

ዶክተር ማክሲም ሁዋኔቶን በበኩላቸው÷ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሴቶችን ለማብቃትና የስርዓተ ፆታ እኩልነትን ለማስፈን እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል፡፡

በቀጣይም ከሚኒስቴሩ ጋር በጋራ እንደሚሰሩና አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.