Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ወደ ኮፐንሃገን በረራ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከግንቦት 22 ቀን 2023 ጀምሮ ወደ ኮፐንሃገን ዴንማርክ አዲስ የመንገደኞች በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡

በረራው ከማክሰኞ እና እሁድ በስተቀር በሣምንት አምስት ጊዜ የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት÷ ወደ ኮፐንሃገን በረራ መጀመሩ ለአየር መንገዱ በሰሜን አውሮፓ እና በደቡብ ስካንዲኒቪያን ወሳኝ መግቢያ በር ይሆናል።

በረራው የአውሮፓና አፍሪካን ትስስር በማሳደግ የንግድ፣ ቱሪዝም እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደሚያጠናክር ተጠቁሟል፡፡

የኮፐንሃገን አውሮፕላን ማረፊያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቶማስ ወልድቢ በበኩላቸው÷ በዴንማርክ እና በአፍሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት የማጠናከር የቆየ ፍላጎት እንደነበራቸው ገልጸዋል፡፡

ላለፉት 5 ዓመታት የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ተብሎ የተሸለመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኮፐንሃገን በረራ ሊጀምር መሆኑ መልካም ዜና ነው ብለዋል።

የበረራው መጀመርም ለዴንማርክ ወደ አፍሪካ ሀገራት መግቢያ በር ይሆናታልም ነው ያሉት።

በረራው ለዴንማርክ ንግድ በተለይም ለፋርማሲው ኢንዱስትሪ አዳዲስ እድሎችን እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኮፐንሃገን በረራ የጀመረው ሕዳር 1999 ቢሆንም በረራው ከአራት ዓመታት በኋላ ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.