Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል 600 ሺህ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የውሃ ፕሮጄክቶች በቅርቡ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንደሚውሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል 600 ሺህ ነዋሪዎችን ጠቃሚ የሚያደርጉ የውሃ ፕሮጄክቶች በቀጣይ ሁለት ወራት ተጠናቀው ለአገልግሎት እንደሚውሉ የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ።

በክልሉ ከዓለም ባንክ በተገኘ ገንዘብ እየተገነቡ ካሉ 20 የውሃ ፕሮጄክቶች ውስጥ 16ቱ ጥሩ አፈፃፀም ላይ እንዳሉ ነው የተገለጸው።

ከአስራ ስድስቱ መካከል ስምንቱ በቀጣይ ሁለት ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንደሚውሉ የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ኢንጅነር መሃመድ ዝያድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ተጠናቀው አገልግሎት የሚውሉት በኤጄሬ፣ ሰጉሬ፣ ዶዶላ፣ ደብረፅጌና ሌሎች የክልሉ ከተሞች እየተገነቡ ያሉ ፕሮጄክቶች ሲሆኑ 600 ሺህ ሰዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ኢንጂነር መሃመድ ገልፀዋል።

በጅማ ዞን ሰቃ ከተማም ከዓለም ባንክ በተገኘ 80 ሚሊየን ብር ሲገነባ የነበረውና 32 ሺህ ነዋሪዎችን የተጠቃሚ የሚያደርገው የውሃ ፕሮጄክት ተናጠናቆ ለአገልግሎት መዋሉ ይታወሳል፡፡

በሙክታር ጠሃ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.