Fana: At a Speed of Life!

ለክልሉ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች እገዛ ወሳኝ ነው – አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለክልሉ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች እገዛ ወሳኝ መሆኑን የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በጋምቤላ ከተማ ከሃይማኖት አባቶችና ከሃገር ሽማግሌ ተወካዮች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ እየመከሩ ነው።

አቶ ኡሞድ ÷ አሁን ያለው ሀገራዊ የለውጥ ምዕራፍ ዘላቂ እንዲሆንና የኢትዮጵያውያን የአብሮነትና የመደጋገፍ እሴት እንዲጎለብት ሁሉም በኃላፊነት መንፈስ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

በተለይም የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የመፍትሄ አካል ሊሆኑ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በክልሉ የሚገኙ ከተሞችን ሰላም አስተማማኝ በማድረግ ለተሻለ ዕድገት እንዲተጉ ለማድረግ የተለያዩ ተቋማት አደረጃጀቶች አበክረው እንዲሰሩ መጠየቃቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.