ኢትዮጵያ ከስንዴ ተመጽዋችነት ወደ ውጭ ገበያ አቅራቢነት ተሸጋግራለች – ግብርና ሚኒስቴር
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በስንዴ ልማት ላይ በቁጭትና ቁርጠኝነት በመሥራት ኢትዮጵያን ከስንዴ ተመጽዋችነት ወደ ውጭ ገበያ አቅራቢነት ማሸጋገሩን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ኢትዮጵያ በየዓመቱ 17 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ከውጭ በማስገባት ከ700 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ የምታደርግበት የታሪክ ምዕራፍ መዘጋቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የስንዴ ልማት ኢትዮጵያን ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ትልቅ የስኬት መንገድ መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
የስንዴ ብዝኅ-ሕይወት መገኛ የሆነችው ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን መቻል አቅቷት ለዘመናት ከውጭ ታስገባ እንደነበር አስታውሰዋል።
በስንዴ ልማት የተመዘገበው ስኬት የአመራሩን፣ የምርምር ተቋማትና የአምራቹን ቁጭትና ቁርጠኝነት ያሳየ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በስንዴ ላይ ዓለም የመሰከረለት ውጤት ስታስመዘግብ ከአመራሩና የዘርፉ ባለሙያዎች ባሻገር የአርሶ አደሩ ተሳትፎ የጎላ እንደነበርም ነው የገለጹት፡፡
የስንዴ ምርትን ከሀገር ውስጥ ፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ ማቅረብ የተቻለው ስንዴን በእርዳታ እንጂ በሰብል ደረጃ አይነቶት የማያውቀው ከፊል አርሶ አደር በፍላጎት መሥራት በመቻሉ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
አርሶ አደሩ መንግሥት የሚያቀርብለትን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ፈቅዶ በመቀበል በቀላሉ ጥቅም ላይ የማዋል ፍላጎትና ተነሳሽነት እንዳለው አይተናል ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!