አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከሱዳን ተጠባባቂ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከሱዳን ተጠባባቂ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ መምከራቸውን አምባሳደር ይበልጣል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በሱዳን ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን አስመልክቶ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡