በትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሊቦ ከምከም ወረዳ አንጎት ቀበሌ ዛሬ ጠዋት 1፡30 ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
አደጋው የደረሰው÷ ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ አንጎት ቀበሌ አንባርጌ አካባቢ ሲደርስ ከባጃጅጋር በመጋጨቱ ነው፡፡
በዚህም በባጃጁ ውስጥ ከነበሩ ተሳፋሪዎች ውስጥ ሁለት ሰዎች ወዲያው ሕይወታቸው ማለፉን የወረዳው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ጉዳት የደረሰባቸው ሌሎች ሁለት ሰዎችም በአዲስ ዘመን የመጀመሪያ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡