Fana: At a Speed of Life!

በተለያየ ሙያ የሰለጠኑ 1 ሺህ 136 ከስደት ተመላሾች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 8 የቴክኒክ እና ሙያ ሥልጠና ኮሌጆች በተለያየ ሙያ የሰለጠኑ 1 ሺህ 136 ከስደት ተመላሾች በዛሬው ዕለት በንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተመርቀዋል።

መንግሥት በመደበው በጀት እና የጀርመን ተራድኦ ልማት ድርጅት ድጋፍ የተመረቁት እነዚሁ ተመራቂዎች በአውቶ መካኒክ፣ በሆቴል እና ቱሪዝም እንዲሁም በልብስ ስፌት እና በሌሎች የሙያ መስኮች ለ6 ወራት ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መሆናቸው ተገልጿል።

ተመራቂዎቹ በማኅበር ተደራጅተው የሥራ ዕድል እንደሚፈጠርላቸው መገለጹን ከአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.