Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ለ500 ሰዎች ማዕድ አጋራ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 1444ኛውን የረመዷን ፆም ምክንያት በማድረግ ዛሬ ለ500 ሰዎች ማዕድ አጋራ፡፡

ለዚሁ መርሐ ግብር አስተዳደሩ ከ6 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

ለእያንዳንዱ አቅመ ደካሞችና አረጋውያን 5 ሊትር ዘይት፣ 25 ኪሎ ዱቄት እና 6 ኪሎ ቴምር ድጋፍ ተደርጓል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ይህ ተግባር ለዜጎቻችን ያለንን ፍቅርና አክብሮት የምንገልፅበት ነው ብለዋል።

የማዕድ ማጋራት ተግባሩ በለውጡ እየተከተልን ያለነው ሰውነትን መሰረት ያደረገ አካሄድ የወለደው ነው ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 1 ሺህ 360 ካርቶን ቴምር ለአቅመ ደካሞችና አረጋውያን ማበርከታቸውም ተገልጿል፡፡

የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብሩ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እንደሚቀጥልም ነው የተጠቆመው፡፡

በዚሁ መሰረትም በቀጣይ የረመዷን ፆም እና የዐቢይ ፆምን ምክንያት በማድረግ እንደ ከተማ ለ166 ሺህ ሰዎች ማዕድ የማጋራት ተግባር እንደሚከናወን ተመልክቷል፡፡

በበረከት ተካልኝ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.