Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ከደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ጋር የባሕር ኃይል ልምምድ ጀመረች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ጥምር የባሕር ኃይል ወታደራዊ ልምምድ ማካሄድ ጀመሩ፡፡

ወታደራዊ ልምምዱ በአሜሪካ የሚመራ ሲሆን፥ በኒውክሌር የሚንቀሳቀሰው የአሜሪካው  አውሮፕላን ተሸካሚ ግዙፍ መርከብ ተሳታፊ መሆኑን አር ቲ ዘግቧል፡፡

ይሄው መርከብ ሀገራቱ ከሰሜን ኮሪያ ባሕር ሰርጓጅ መርከብ ባለስቲክ ሚሳኤል ቢተኮስባቸው እንዴት እንደሚመክቱ መለማመድ የሚያስችል ሙሉ አገልግሎቶች ተሟልተውለታል ተብሏል፡፡

ልምምዱ ለሁለት ቀናት ጀጁ በተሰኘችው የሴኡል ደቡባዊ ደሴት እንደሚካሄድ የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከሰሜን ኮሪያ የሚቃጣ ማንኛውንም ጥቃት በብቃት መመከት እንችላለን ሲሉ ደግሞ በልምምዱ ላይ እየተካፈሉ የሚገኙት የደቡብ ኮሪያ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ኪም ኢን-ሆ ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.