በመዲናዋ ለሚካሄደው የጎዳና ላይ ኢፍጣር የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የረመዳን ጾምን አስመልክቶ ነገ በአዲስ አበባ የሚደረገው የጎዳና ላይ ኢፍጣር በሰላም እንዲካሄድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁ አስታውቋል፡፡
“ኢፍጣራችን ለወገናችን” በሚል መሪ ቃል ነገ ቅዳሜ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከባምቢስ በመስቀል አደባባይ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ ባለው ጎዳና ላይ የኢፍጣር ፕሮግራሙ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
ፕሮግሙ በሚካሄድበት ወቅት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠርም፡-
* ከቅዱስ ኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
* ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
* ከአራተኛ ክፍለ ጦር ወደ መስቀል አደባባይ
* ከልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፣ በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ
* ከጎማ ቁጠባ ወደ መስቀል አደባባይ
* ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ
* ከካዛንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ
* ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ መስቀል አደባባይ
* ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
* ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ መስቀል አደባባይ
* ከሜትሪዎሎጂ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ከቀኑ 6:00 ሠዓት እስከ ምሽት 2:00 ሠዓት ድረስ ድረስ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ስለሆነም አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡