Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን በፅኑ መሰረት ላይ ለመገንባት ወጣቶች ሀገራቸውን እንዲያውቁ ማድረግ ይገባል -አቶ ታዬ ደንደኣ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን በፅኑ መሰረት ላይ ለመገንባት ወጣቶች ሀገራቸውን እንዲያውቁ እና እርስ በርስ እንዲቀራረቡ ማድረግ ይገባል ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደኣ ተናገሩ፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለስድስት ዙር ያሰለጠናቸውን 6 ሺህ 714 ብሄራዊ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደኣ፥ የሰላም ሚኒስቴር ወጣቶችን አንድ ቦታ ላይ እንዲገናኙ በማድረግ እሴቶችን ተለዋውጠው ልዩነቶችን አቻችለው በሰላም እንዲኖሩ የሚያስችል ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያን በፅኑ መሰረት ላይ ለመገንባት ወጣቶች ሀገራቸውን እንዲያውቁ እና እርስ በእርስ እንዲቀራቡ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን የተናገሩት አቶ ታዬ በዚህ ረገድ ብሔራዊ በጎ ፈቃደኞች ሰፊ ሚናን እየተጫወቱ ነው ብለዋል።

ሰልጣኝ ወጣቶችም ሀገራቸውን በወሰዱት ስልጠና እንዲያገለግሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

እንዲሁም በባህርዳር ዩንቨርሲቲ ለሰላሳ ቀናት ሲሰለጥኑ የቆዩ ከ1 ሺህ 600 የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ሰልጣኞች ስልጠናቸውን በስኬት አጠናቀዋል፡፡

በሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና የግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መስፍን (ዶ/ር) በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ስምሪት የሚሰጣችሁ የሰላም መልዕክቶች የሰላም አምባሳደር በመሆን በዘላቂ ሰላምና ሀገራዊ መግባባት ስራ ውስጥ የራሳችሁን ዐሻራ እንድታሳርፉ አሳስባለሁ ብለዋል፡፡

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስልጠና የወሰዱ 1 ሺህ 788 ወጣቶች ስልጠናውን በስኬት አጠናቀው ተመርቀዋል፡፡

በሰላም ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴዔታ ማዕረግ የሚኒስትር አማካሪ ካይዳኪ ገዛኸኝ በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ተመራቂዎች የማኅበረሰቡን ባህል፣ ታሪክ፣ እሴትና አኗኗር በመረዳት ያደጋችሁበትን ማኅበረሰብ ልምድ በማካፈል ለብሔራዊ መግባባት፣ ለሀገራዊ አንድነትና ለሰላም መስፈን የበኩላችሁን ሚና ልትወጡ ይገባል ብለዋል፡፡

በወርቃአፈራው ያለው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.