ዓመታዊ የኢንቨስትመንት ፎረም በያዝነው ወር በመዲናዋ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2 ፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ)”ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023” ዓመታዊ የኢንቨስትመንት ፎረም ከሚያዝያ 18 እስከ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለፀ፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን÷ ፎረሙን በማስመልከት ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
የኢንቨስትመንት ፎረሙ አላማ ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት አማራጮች ለዓለም አቀፍ ባለሀብቶች ማስተዋወቅ መሆኑን ገልጸዋል።
በፎረሙ ከ600 በላይ የውጭ ባለሀብቶች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አቶ ተመስገን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ፎረሙ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡