Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ልዩ ኃይሉን መልሶ የማደራጀት ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ክልል ልዩ ኃይሉን መልሶ የማደራጀት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በመንግሥት በተጠናው የልዩ ኃይል አደረጃጀታዊ መዋቅር መሠረት ወጥ የሆነ የጸጥታ ኃይል ማደራጀት ተገቢ መሆኑ ተመላክቶ ሥራው መከናወኑን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዓለማየሁ ማሞ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ልዩ ኃይሉ በብሔርና በክልል ደረጃ ተዋቅሮ መቆየቱ የመደበኛ የፖሊስ ተግባርን በእጅጉ ያዳከመ ነበር ብለዋል፡፡

በብሔር መደራጀቱ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች አጋጥሞ የነበረውን የፀጥታ ችግር መፍታት ከባድ አድርጎት እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡

አያይዘውም የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት በተቀመጠው አማራጭ መሰረት በፍላጎት እና መርጠው ድልድሉ መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡

የማደራጀቱ ሥራ መቀጠሉንም ነው የተናገሩት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.