Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት የኮሚቴዎች ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት የኮሚቴዎች ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
 
ስብሰባው በቀጠናው እና በአካባቢው ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የሚደረገውን የፖሊስ እንቅስቃሴ የማሳደግ ዓላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
ለሶስት ቀናት በሚቆየው ስብሰባ የህብረቱ የፀረ-ሽብር፣ የህግ፣ የስርዓተ – ጾታ፣ የሳይበር እና የስልጠና ኮሚቴዎች አባላት ተሳትፈዋል፡፡
 
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካኤል 14 አባል ሀገራት ያሉት የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ናቸው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.