በድሬዳዋ የሚገነባው የሲሚንቶና ብረት ፋብሪካ የግንባታ እቃዎችን እጥረት ይፈታል -ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ የሚገነባው የሲሚንቶ፣ ብረትና ኖራ ፋብሪካ የወቅቱ ፈተና የሆነውን የግንባታ እቃዎች እጥረት ይፈታል ሲሉ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ገለጹ፡፡
ናሽናል ዌስት ኢንተርናሽናል ሆልዲግ በድሬዳዋ የሚያስገነባው የሲሚንቶ፣ ብረትና ኖራ ፋብሪካ 540 ሚሊየን ዶላር አጠቃላይ ወጪ ተደርጎበት የሚገነባ ሲሆን÷ በዛሬው ዕለትም የ243 ሚሊየን ዶላር የመጀመሪያ ዙር የግንባታ ውል ተፈርሟል።
ወ/ሮ ጫልቱ በግንባታ ስምምነት ላይ እንደተናሩት÷ ኩባንያው ከፍተኛ የፕሮጀክት አስተዳደር ስርዓት ያለው ግዙፍ ተቋም ነው፡፡
ሚኒስቴሩ የግንባታ ግብዓቶችን አምራች ኢንዱስትሪዎችን የማበረታታትና የመደገፍ ስልጣን እንደተሰጠው ገልጸው÷ምርት በብዛት እንዲመረትና ገበያው እንዲዘምን በማድረግ ሀላፊነታችንን እንወጣለን ብለዋል።
በድሬዳዋ የሚገነባው የሲሚንቶ፣ ብረትና ኖራ ፋብሪካ የወቅቱ ፈተና የሆነውን የግንባታ እቃዎች እጥረት የሚፈታ ይሆናልም ነው ያሉት ።
የናሽናል ዌስት ኢንተርናሽናል ሆልዲን የሀገር ውስጥ የምርት ፍጆታን በለሚ ናሽናል በመሸፈን በመልካ ጀብጁ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት የሚችል እንደሆነም አንስተዋል፡፡
ኩባንያው የስራ እድል ከመፍጠርና የውጭ ምንዛሬ ከማስገኘት ባለፈ የኢትዮጵያ መልካም ገጽታ የሚያስተዋውቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ፋብሪካው ሲጠናቀቅ በዓመት 3 ሚሊየን ቶን ሲሚንቶና 700 ሺህ ቶን ብረት የማምረት አቅም ያላቸው እንዳለው ተጠቁሟል፡፡
በቤተልሄም መኳንንት