Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም ጥቁር ህዝቦች ታሪክ ቅርስና ትምህርት ማዕከል አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም ጥቁር ህዝቦች ታሪክ ቅርስና ትምህርት ማዕከል አባላት ጋር ተወያዩ፣

መቀመጫውን በለንደን ያደረገው የዓለም የጥቁር ህዝቦች የታሪክ ቅርስና ትምህርት ማዕከል ዋና ጽህፈት ቤቱን በአዲስ አበባ መክፈት እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡

የማዕከሉ አባላት ዛሬ ከአቶ ደመቀ መኮንን ጋር ባደረጉት ውይይት ማዕከሉ ጽህፈት ቤቱን አዲስ አበባ ውስጥ የሚከፍተው ኢትዮጵያ አፍሪካ በጥቁር ህዝቦች ታሪክ እና ነፃነት ውስጥ ቁልፍ ሚና ስላላት ነው ብለዋል፡፡

የአፍሪካውያን የዘመናት ስርዓተ-ታሪክ እና ባህል አንድ ቦታ መሰባሰብ እንዳለበት ጠቅሰው ኢትዮጵያ ለዚህ ሁነኛ ሀገር መሆኗን ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ኢትዮጵያ ለማዕከልነት በመመረጧ አመስግነው መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.