የኢትዮ – አሜሪካ የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በአሜሪካ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ አሜሪካ የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በአሜሪካ የውጭ ግንኙነት ምክር ቤት እየተካሄደ ነው።
በፎረሙ ላይ የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
በፎረሙ ወደ 100 የሚጠጉ ከሁለቱ ሀገራት የተውጣጡ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች ተሳታፊ ናቸው።
በባንክ እና ፋይናንስ ከተሰማሩና እንደ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ጋር በተያያዘ ጠቃሚ ውይይት መደረጉም ነው የተገለጸው።
በዚህ ወቅትም ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የማምረቻውን ዘርፍ ጨምሮ በግብርናው፣ በማዕድን፣ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን፣ ቱሪዝም፣ ጤና፣ በኃይል እና ንግድ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸው ተመላክቷል።
የፎረሙ ተሳታፊዎች አሜሪካ የኢትዮጵያን የአጎዋ ተጠቃሚነት እንድትመልስላት ጠይቀዋል።