ሩሲያ በባክሙት የዩክሬን ወታደሮች ተቆርጠው መቅረታቸውን አስታወቀች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በባክሙት ከተማ የዩክሬን ወታደሮች ተቆርጠው መቅረታቸውን አስታውቃለች፡፡
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ በባክሙት ተቆርጠው የቀሩት የዩክሬን ወታደሮች በሩሲያ ሃይሎች ከበባ ውስጥ መግባታቸውን አረጋግጧል፡፡
የሩሲያ አየር ወለድ የተቆረጡት የዩክሬን ወታደሮች ምንም አይነት መውጫ እና ድጋፍ እንዳያገኙ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ዩክሬን በበኩሏ÷ ወታደሮቿ ተቆርጠዋል የሚለውን መረጃ ውድቅ በማድረግ በስፍራው ከሚገኙት ወታደሮች ጋር እስካሁን ግንኙነት መኖሩን አስታውቃለች፡፡
የዩክሬን ወታደሮች በባክሙትን መልሶ ለመቆጣጠር የተጠናከረ ዘመቻ መክፈታቸውንም አልጀዚራ በዘገባው አስፍሯል፡፡