Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የጋራ ስብሰባ በድሬዳዋ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የጋራ ስብሰባ የሁሉቱም ክልል ርዕሳነ- መስተዳድሮች በተገኙበት በድሬዳዋ ከተማ ተካሂዷል፡፡

ሁለቱ ክልሎች በሰባት ዞኖች የሚዋሰኑ እና ለረዥም ዘመናት የጋራ ባህል እና ታሪክ ተጋርተው የኖሩ ህዝቦች መሆናቸውን የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ተናግረዋል፡፡

ቀደም ሲል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅግጅጋ ከተማ ኢፋቦሩ ትምህርት ቤት በማስገንባት ማስመረቁንም አስታውሰዋል፡፡

የህዝቦችን ወንድማማችነት ለማጠናከር አመራሩ በጋራ ማቀድ እና ህዝብን ማሳተፍ፣ የሁለቱን ክልሎች ድንበር በማካለል ሂደት ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን በጋራ በውይይት መፍታት እና የተቀናጀ የጋራ ፕሮጀክቶችን ማጠናከር እንደሚገባ አቅጣጫ መቀመጡንም ገልጸዋል፡፡

ከመጪው ሳምንት ጀምሮ የየክልሎቹ አመራር እና ህዝብ በየደረጃው ተገናኝተው በጋራ የልማት ስራዎች ላይ እንደሚሳተፉም ነው ያነሱት፡፡

የሶማሌ ክልል የብልጽግና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መሐመድ ሻላ በበኩላቸው÷ ከዚህ በፊት የነበሩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እንዲሁም የሁለቱን ህዝቦች ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ውይይት በጅግጅጋ ከተማ መካሄዱን አስታውሰዋል፡፡

በዚህ ውይይት የሁለቱን ክልል አመራር ከዚህ ቀደም የነበሩ ችግሮችን በመፍታት በቀጣይም መሰል ችግሮችን በውይይት መፍታት እንደሚቻል መስማማታቸውን ኦ ቢ ኤን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.