የሀይማኖት አባቶች ለትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የተገኘውን ሰላም፣ ክርስቲያኑ ምዕመን በጎ ተግባራትን በማከናወን ሊተገብር እንደሚገባ የሀይማኖት አባቶች አሳሰቡ።
የሀይማኖት አባቶቹ የትንሣኤ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ለሰው ልጅ ደህንነት፣ ሰላም የተገኘበት መሆኑን ገልጸዋል።
ክርስቲያኑ ምዕመን ለሀገር ሰላምና፣ አንድነት መረጋገጥ ተግቶ ሊሰራ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
በኢትዮጵያ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የሰላም መደፍረስ ችግሮች በውይይት እና በመግባባት ሊፈቱ እንደሚገባ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
በዓሉን ከችግረኛ ወገኖች ጋር አብሮ ማሳለፍ እንደሚገባም ነው የሀይማኖት አባቶቹ ያሳሰቡት።