የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ የነበራቸውን የሥራ ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂዮ ሜሎኒ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የሥራ ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂዮ ሜሎኒ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂዮ ሜሎኒ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በታላቁ ቤተ መንግስት የክብር የእራት ተጋብዘዋል፡፡
በተጨማሪም ሚኒስትሯ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ጋር የሶስትዮሽ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸውም ሀገራቱ ያላቸውን የሶስትዮሽና ባለብዙ ወገን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር መስማማታቸው ነው የተገለጸው፡፡